ቢስሊማሂረህማን ረሂም
ሁለት ሙስሊሞች ከ2 ወይም ከ3 ወራት መራራቅ (lockdown) ቡሀላ ሲገናኙ ደስታቸው በጣም ንፁህ ውብ እና ስሜታዊ ነው። ሲገናኙ በሱናው መሰረት ለመጨባበጥ ለመተቃቀፍ እንደ ሶሀባዎች (ረዐ) ሰላምታ ለመሰጣጣት ያላቸው ጉጉት ልዮ ነው ;ድንቅ ነው። እነዚህ እጆች በተገናኙ ሰዐትም አላህ (ሱወ) ይደሰታል ምህረትም ያደርግላቸዋል ልክ ቅጠሎች ከዛፍ ላይ እንደሚረግፉ ሁሉ ወንጀላቸውም ይራገፈል ; ይህ አጋጣሚ አንድን ሙእሚን በደንብ ይገልፀዋል, አንድ ሙእሚን በውስጡ ያለውን የሚወደውን የሚያፈቅረውን የረሱል (ሰወወ) ሱና እያወቀ በፍፁም አይዘነጋም ምንም ነገር ቢፈጠር ከረሱል (ሰወወ) የሱና መንገድ አይወጣም አይዘናጋም ።
በክርን መነካካት፣ እንደሞኝ መጎሻሻም በፍፁም ሱናን አይተኩም ! ተወዳጁ ሱና መጨባበጥ ነው። የረሱል (ሰወወ) ወዳጅ ነኝ ብሎ ነገር ግን የካፊርን ሱና መከተል አግባብ አይደለም ካፊሮች አዘዋል ብለን መታዘዝ እነሱ ያሉትን መተግበር አግባብ አይደለም።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: إِنَّ الْمُسْلِمَ إِذَا صَافَحَ أَخَاهُ تَحَاتَّتْ خَطَايَاهُمَا كَمَا يَتَحَاتُّ وَرَقُ الشَّجَرِ
1: አቡ ሁረይራ (ረዐ) እንደዘገቡት የአላህ መላክተኛ (ሰወወ) አሉ :- ” በእርግጥም ሙስሊሞች እጅ ለእጅ በተጨባበጡ ጊዜ ቅጠሎች ከዛፍ ላይ እንደሚረግፉት ሁሉ የነሱም ወንጀል ይራገፋል”
ምንጭ:- musnad al-Bazzar 8335,Tergheeb 3:433
عَنْ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: مَا مِنْ مُسْلِمَيْنِ يَلْتَقِيَانِ فَيَتَصَافَحَانِ إِلَّا غُفِرَ لَهُمَا قَبْلَ أَنْ يَفْتَرِقَا
2- አል ባራእ ኢብን አዚድ እንደዘገቡት ; የአላህ መላክተኛ (ሰወወ) አሉ:- “ሁለት ሙስሊሞች እጅ ለእጅ አይጨባበጡም እጆቻቸው ከመለያየታቸው በፊት ምህረትን አድርጎላቸው ቢሆን እንጂ”
ምንጭ:- suman al-Tirmidhi 2727
عَنْ أَنَسٍ: قَالَ: كَانَ أَصْحَابُ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا تَلَاقَوْا تَصَافَحُوا، وَإِذَا قَدِمُوا مِنْ سَفَرٍ تَعَانَقُوا
3- አናስ (ረዐ) እንደዘገቡት የረሱል (ሰወወ) ባልደረቦች በተገኙ ጊዜ እጅ ለእጅ ይጨባበጡ ነበር ከጉዞም የተመለሱ እንደሆነ ይተቃቀፉም ነበር”
ምንጭ፡- Al- mu’jam al- Awsat. 97, al- Targheeb 3:3433..
እኛ ምርጥ የሆነ ሀብት ባለቤቶች ነን ልንከተለው ልንተገብረው ልንኖረው ሚገባ ውርስ(legacy) ባለቤቶች ነን እርሱም የተወዳጁ ነቢ (ሰወወ) ሱና ነው። ዛሬላይ ምንመርጠው ምርጫ ነገ ለትውልድ ምናስተላልፈው ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል በሂወታችን ውስጥ የማይታወቅ ባህልን ማምጣት እንፈልጋለን? ወይስ ለትውልድ ለረሱልን (ሰወወ) ተወዳጅ ሱናዎች ማስተላለፍ እንፈልጋለን?? የረሱልን (ሰወወ) ሱና መከተል በሱናቸው መሰረት መኖር ነገ ረሱልን (ሰወወ) በምንገናኝበት ጊዜ ሁሉም ሰው ሱናን መከተል አደጋ (risk)አለው በሚሉበት ወቅት እኛ ግን በሱናተው ላይ መፅናታችንን የምናሳይበት እድሉ አለን።
አላህ (ሱወ) በተወዳጁ ነቢ (ሰወወ) ሱና ላይ የመፅናት ክብርን ያጎናፅፈን።