ቢስሊማሂረህማን ረሂም
ሁለት ሙስሊሞች ከ2 ወይም ከ3 ወራት መራራቅ (lockdown) ቡሀላ ሲገናኙ ደስታቸው በጣም ንፁህ ውብ እና ስሜታዊ ነው። ሲገናኙ በሱናው መሰረት ለመጨባበጥ ለመተቃቀፍ እንደ ሶሀባዎች (ረዐ) ሰላምታ ለመሰጣጣት ያላቸው ጉጉት ልዮ ነው ;ድንቅ ነው። እነዚህ እጆች በተገናኙ ሰዐትም አላህ (ሱወ) ይደሰታል ምህረትም ያደርግላቸዋል ልክ ቅጠሎች ከዛፍ ላይ እንደሚረግፉ ሁሉ ወንጀላቸውም ይራገፈል ; ይህ አጋጣሚ አንድን ሙእሚን በደንብ ይገልፀዋል, አንድ ሙእሚን በውስጡ ያለውን የሚወደውን የሚያፈቅረውን የረሱል (ሰወወ) ሱና እያወቀ በፍፁም አይዘነጋም ምንም ነገር ቢፈጠር ከረሱል (ሰወወ) የሱና መንገድ አይወጣም አይዘናጋም ።
በክርን መነካካት፣ እንደሞኝ መጎሻሻም በፍፁም ሱናን አይተኩም !…
Read More »